የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቻርለስ ሚሼል ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

February 19, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱን አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”ከቻርለስ ሚሼል ጋር በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ወቅት ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል “ብለዋል።

በሰላም ስምምነቱ ላይ በነበረው የመንግሥት ሚና፣ በልማት ሥራዎች እና በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኅብረት ግንኙነት ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡