ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት፣ ከሊቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እና ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በውይይታቸው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስፍረዋል፡፡