Fana: At a Speed of Life!

አቶ አወል አርባ በሀንሩካ ወረዳ የእርሻ ልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ልዑክ በገቢ ረሱ/ዞን/ ሀንሩካ ወረዳ የእርሻ ልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።

አቶ አወል በጉብኝቱ ወቅት በወረዳው የለማን የስንዴ ምርት በኮምባይነር የመሰብሰብ ሂደት አስጀምረዋል፡፡

በተጨማሪም የቅድመ ዝግጅት ስራው የተጠናቀቀውን በ250 ሄክታር መሬት ላይ የለማን የሙዝ እርሻ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በሀንሩካ ወረዳ 1 ሺህ 712 ሄክታር ስንዴ፣ 221 ሄክታር የእንስሳት መኖ እና 430 ሄክታር ሽንኩርት በመመረት ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የክልሉ መንግስት ለእርሻ ልማት ልዩ አቅጣጫ በማስቀመጥና የተቀናጀ እና የተናበበ ትኩረት በመስጠት በተለያዩ ክላስተሮች ምርት የመሰብሰብ ሒደት መጀመሩን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.