Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ለጤና አገልግሎት መሻሻል የጀፓን መንግስት ድጋፍ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት እንዲሻሻል የጀፓን መንግስት ድጋፉን ይቀጥላል ሲሉ በኢትዮጵያ የጀፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ተናገሩ፡፡

አምባሳደሯ የጃፓን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ኢቶ ታካኮ ይህን ያሉት በእንጅባራ ከተማ በ60 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በስርዓተ ጾታ ላይ ያተኮረው የአንድ ዓመት ፕሮጀክት ይፋ በሆነበት ወቅት ነው።

በዚህ ወቅትም የጃፓን መንግስት የኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት እንዲሻሻል የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስና የባለሙያ የስልጠና እገዛ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

የጃፓን መንግስት በቀጣይም በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የተጠናከረ ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት ።

ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ተፅዕኖ የደረሰባቸውን እናቶች፣ ሴቶችና ህፃናት የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

ዩ ኤን ኤፍ ኤ የተባለው ድርጅት ፕሮግራሙ በተሟላ መንገድ ተፈፃሚ እንዲሆን ኃላፊነት እንደተሰጠው ነው የተገለጸው።

ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል 8 ወረዳዎች በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሁለት ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

የሁለቱ ክልሎች የጤና ቢሮ ተወካዮች በበኩላቸው÷ የጃፓን መንግስት ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች የደረሰውን ማህበራዊ ቀውስ በመገንዘብ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን አመስግነዋል፡፡

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.