Fana: At a Speed of Life!

50 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሕንድ በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 50 የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሕንድ በተዘጋጀው የአራት ቀናት የሥልጠና መርሐ-ግብር ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ልዑካን ቡድኑ የኢፌዴሪ መንግስት ዋና ተጠሪዎችን ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ምክትል ሰብሳቢዎች፣ የክልል ፓርላማ ፕሬዚዳንቶች በአጠቃላይ 50 የኢፌዴሪ ፓርላማ አባላትን ያቀፈ ነው ተብሏል፡፡

መርሐ ግብሩ በሕንዱ የዴሞክራሲዊ ፓርላማ ጥናት እና ሥልጠና ኢኒስቲትዩት የተዘጋጀው መሆኑን በኢትዮጵያ የሕንድ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ልዑካኑ ሕንድ ኒው ዴልሂ ሲደርሱ በሀገሪቱ የኢትጵያ አምባሳደር እና የሕንድ ማኅበረሰብ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.