የሀገር ውስጥ ዜና

በአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ የተሳተፉ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተሸኙ

By Melaku Gedif

February 20, 2023

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ መጠናቀቅን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም የኬንያ፣ ሴኔጋል ፣ ሩዋንዳ፣ ሞሮኮ፣ ማዳጋስካር፣ አልጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ቻድ ፣ጋና ቦትስዋና፣ ናይጄሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሲሸልስ እና ብሩንዲ መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በተጨማሪም የሌሴቶ፣ አንጎላ፣ ጋቦን፣ ጅቡቲ፣ ኒጀር፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ፍልስጤም እና የሴራሊዮን መሪዎች ወደ ሀገራቸው ማቅናታቸው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የተለያዩ ሚኒስትሮችም ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡

ቀሪዎቹ መሪዎችም ዛሬ ማምሻውን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡