Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በገልፍ ፉድ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ዱባይ በገልፍ ፉድ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈች ነው፡፡

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታው ካሳሁን ጎፌ በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ከ6 ሺህ በላይ የንግድ አንቀሳቃሾች በሚሳተፉበት በዚህ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ኤክስፖርተሮች በበቂ ዝግጅት እንዲሳተፉ የማስተባበር ስራ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ መከናወኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ የሚተዋወቅበት ፓቪሊዮንም ተመርቆ መከፈቱን አቶ ካሳሁን በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ለአምስት ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽን÷ ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ የግብይት ኮንትራት እንደሚፈረም ይጠበቃል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.