የተመድ የልማት ፕሮግራም የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቢሮ ሃላፊ አሁና ኢዚያኮንዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በአጠቃላይ በተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ መክረዋል፡፡
በሰላም ግንባታ ሒደት ስራዎች ላይ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና በቅርቡ የተቋቋመው ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ስራ ውጤታማነት ላይ በጋራ ለመስራት በትኩረት መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡
አሁና ኢዚያኮንዋ÷የተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ ) በሰላም ግንባታ ሂደት ስራዎች ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እና በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ትጥቅ የማስፈታት፣ የማገገም፣ የመልሶ ግንባታና ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት የመመለስ ተግባራት በጋራ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው÷ ዩ ኤን ዲፒ ለኢትዮጵያ እያደረገ ላለው ድጋፍና ትብብር ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!