በመዲናዋ ዓለም አቀፍ የእምነት ተቋማት ትብብር ጉባዔ ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የእምነት ተቋማት ትብብር ጉባዔ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አስታወቀ፡፡
የጉባዔው ዓላማ ÷ በቤተ እምነቶች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ በአማኞች መካከል መግባባትን ማጎልበት ነው፡፡
የሃይማኖት ተቋት ጉባዔ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ የዓለም አሁናዊ ፈተናዎች ላይ ምክክር ያደርጋል የተባለው ጉባዔው ለፖሊሲ አውጪዎች የመፍትሄ ሀሳቦችን ያቀርባል።
ጉባዔው በየዓመቱ ከአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ማግስት እንደሚካሔድም ተገልጿል።
በወንድሙ አዱኛ