የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሱዳን የሉዐላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተና ጀነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

April 09, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን ጋር በስልክ ተወያዩ።

በነበራቸው ቆይታም ለኮቪድ19 ቀውስ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በቅርበት ስለ መሥራት ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።