የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ገባ

By ዮሐንስ ደርበው

February 21, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ ገብቷል።

ልዑኩ በቆይታው በሀገራቱ የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ከሀገሪቱ የገንዘብ ተቋማት እና የኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ጋር ስትራቴጂካጂካዊ ውይይት እንደሚያደርጉ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቋል።

በተጨማሪም ልዑኩ በሀገራቱ የጋራ ኢኮኖሚ እና የንግድ ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው የኢትዮ ቻይና የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እንደሚሳተፍም ነው የሚጠበቀው።

ልዑኩ አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ፥ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሌሊሴ ነሜ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችን ያካተተ ነው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!