የሀገር ውስጥ ዜና

የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ ተራዘመ

By Feven Bishaw

February 21, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንዲችሉ ቀኑ መራዘሙ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡