በ44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለተሳተፈው ቡድን የማበረታቻ ሽልማት ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የእውቅና እና ማበረታቻ ሽልማት ተደረገለት።
የአትሌቲክስ ቡድኑ ከዓለም በ2 ወርቅ፣ በ7 ብር እና በ1 ነሐስ በጠቅላላው 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 2ኛ ደረጃን በመያዝ ተመልሷል።
ልዑኩ ትናንት ሌሊት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ አቀባበል እንተደረገለት የየባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሽልማቱ መሠረትም ፌዴሬሽኑ ለወርቅ 45 ሺህ፣ ለብር 30 ሺህ፣ ለነሃስ 15 ሺህ፣ ለዲፕሎማ 10 ሺህ እና ለተሳትፎ 5 ሺህ ብር ለእያንዳቸው ሸልሟል።