Fana: At a Speed of Life!

ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በልደታ ክፍለ ከተማ  ሳር ቤት አካባቢ እንደ አዲስ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ስራ አስጀምረዋል፡፡

የስፖርት ማዘውተሪያው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እና በሁሉም የበቃ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በአካል፣ በሥነ ምግባር እና በሥነ ልቡና የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የሚያግዝ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ገንብተናል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል ሲሉም ገልፀዋል።

በየአካባቢው ተመሳሳይ የስፖርት ማዕከላትን እያስፋፋን እንቀጥላለንም  ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.