Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ ሁሉም የድርሻዉን ሊወጣ ይገባል- የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 1፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)ኢትዮጵያ ይፋ ያደረገችዉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ ሁሉም የድርሻዉን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸዉ  የሶሻል ዲሞክራቲክ ፣ ኢዜማ እና የትግራይ ዲሞክራቲክ ፓርቲ አመራሮች÷ ኮቪድ  19 ካለዉ አሳሳቢነት አንጻር የተደራጁ የቅንጅት አሰራሮች  ይጠበቃሉ ብለዋል።

የሶሻል ዲሞክራቲክ እና የትግራይ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመናብርት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስና ዶክተር አረጋዊ በርሄ፣ ቫይረሱን በተመለከተ የሚስተዋሉ መዘናጋቶችን በህጋዊ ማእቀፍ መስመር ለማስያዝ የአዋጁ መደንገግ ተጠባቂ ነበር ብለዋል፡፡

የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ በበኩላቸው  አዋጁ ዜጎችን ከበሽታ  የመታደግ አላማ በመሆኑ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም  ብለዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ የአዋጁን አላማ ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበትም ነዉ ያሉት ፡፡

በአዋጁ ተግባራዊነት ሂደት ዉስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ዉስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ችግር እንዳያጋጥማቸዉ የተጀመሩ የትብብር ስራዎች ሊጠናክሩ እንደሚገባም አመራሮቹ አንስተዋል  ፡፡

ከዚያም ባለፈ ለተሻለ ነገ ከባለሙያዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸዉ አካላት እየተላለፉ ያሉ  የጥንቃቄ መልእክቶች ቸል ሊባሉ እንደማይገባም ነው የገለጹት፡፡

በአወል አበራ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.