የሀገር ውስጥ ዜና

ትኩረቱን ፓን አፍሪካኒዝም ላይ ያደረገ መድረክ ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

February 22, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ትብብር የተዘጋጀና ፓን አፍሪካኒዝም ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወጣት ቢሆንም የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የፓን አፍሪካኒዝም ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የፅሁፍ ስራዎች መታተማቸውን አስረድተዋል።

በመድረኩ ላይ እውቁ ፕሮፌሰር ሀኪም አሊ “የአፍሪካ ዳያስፖራ እና የአፍሪካ እድገት” በሚል ርእስ ፅሁፍ አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር ሀኪም በፅሁፋቸው ላይ የፓን አፍሪካኒዝምን ምንነት እና ታሪክ አንስተዋል።

በተጨማሪም አፍሪካውያን ዳያስፖራዎች ለአህጉሪቱ እድገት የሚኖራቸው ሚና የሚናቅ ባለመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

መሰል መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።

በፍቅርተ ከበደ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!