Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከተለያዩ የቻይና ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በቻይና በተለያዩ ዘርፎች ላይ ከተሠማሩ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቤጂንግ ተወያዩ፡፡

ኮሚሽነር ሌሊሴ ÷ በፋርማሲዩቲካልስ፣ በግንባታ ዕቃዎች እና በሲሚንቶ ማምረቻ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ከተሰማሩ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ነው በተናጠል የመከሩት፡፡

ኮሚሽነሯ ኢትዮጵያ በተጠቀሱት ዘርፎች ያላትን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና አማራጮች ማብራራታቸውን በቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

የፋርማሲዩቲካልስ ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነሯ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት እድሎችም አብራርተዋል፡፡

የቂሊንጦ ፋርማሲዩቲካልስ አንዱስትሪ ፓርክ ዘመናዊና ሁሉን-አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ በዘርፉ የሚሰማሩ ኩባንያዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ምርት እንዲገቡ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ነው የገለጹት።

በኢትዮጵያ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው ኩባንያዎችም ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽነሯ ከSINOMA Engineering እና SINOMA Cement Co. Ltd. ፕሬዚዳንቶች ጋር ባደረጉት ውይይት፥ በኢትዮጵያ ባለው ከፍተኛ የኮንስትራክሽን እንቅስቃሴ ምክንያት በግንባታ እቃዎች እና ሲሚንቶ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠን መኖሩን ገልጸዋል፡፡

ይህም በዘርፉ ለሚሰማሩ የቻይና ኩባንያዎች ከፍተኛ የኢንቨስትመንት እድል ይሰጣል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ ላይ እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽጾ አመስግነው በማምረቻ የኢንዱስትሪ ዘርፍ በይበልጥ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.