በግማሽ ዓመቱ ለተከናወኑ ሥራዎች 26 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል- የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተጠናቀቀው ሥድስት ወር ላከናወናቸው ሥራዎች 26 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር ወጪ ማድረጉን ገለጸ፡፡
397 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ እንዲሁም በመደበኛ፣ ወቅታዊ እና ከባድ ጥገና 5 ሺህ 123 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና ሥራ መከናወኑን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አስተዳደሩ ባለፉት ሥድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም እና በቀጣይ ሥራዎች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ ህብረተሰቡን በቅርበት ለማገልገል እና የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በቅርበት ለመቆጣጠር ታስቦ በአዲስ መልክ ከተደራጁት 27 የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤቶች መካከል 25 በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
በግማሽ ዓመቱም የ14 መንገድ ፕሮጀክቶች እና የ19 ግንባታ ቁጥጥር ግዥ መፈፀም መቻሉም ተመላክቷል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ግጭት፣ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ የፀጥታ ስጋቶች፣ ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች በግማሽ ዓመቱ ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም የሥራ ተቋራጮች አቅም ማነስ እንዲሁም የግንባታ ግብዓት እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት በግንባታ ፕሮጀክቶቹ ሂደት ላይ መስተጓጎል መፍጠሩ ነው የተገለጸው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!