በቦረና ካሉት የቀንድ ከብቶች 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል ተባለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር እንደሚያስፈልግ የዞኑ አስተዳደር ገለጸ፡፡
በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎቹ የቀንድ ከብቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የቀሩትን 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ለመታደግ እየተሰራ ሲሆን ፥ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ቢሆንም ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ መሆኑን ነው የዞኑ አስተዳደሪ ጃርሶ ቦሩ የገለጹት።
እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የታሰበውን ያህል ችግር ውስጥ የሚገኙ ከብቶችን መታደግ ከባድ ሊሆን እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡
እስካሁን ዞኑ በቀንድ ከብቶች ሞት ምክንያት33 ቢሊየን የሚገመት ብር ማጣቱንም አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡
በታሪኩ ለገሰ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!