በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የኦሮሚያ ክልልን የመንገድ ሽፋን ከ61 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ለማድረስ እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው በጀት ዓመት መጨረሻ የኦሮሚያ ክልልን የመንገድ ሽፋን 61 ሺህ 513 ነጥብ 97 ኪሎ ሜትር ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ መንገዶችና ሎጅስቲክስ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ሔለን ታምሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ በተጠናቀቀው ግማሽ በጀት ዓመት 413 ነጥብ 88 ኪሎ ሜትር አዲስ የመንገድ ግንባታ ተከናውኗል፡፡
በዚህም ባለፈው ዓመት 58 ሺህ 981 ነጥብ 30 ኪሎ ሜትር የነበረው የክልሉ የመንገድ ሽፋን 59 ሺህ 381 ነጥብ 33 ኪሎ ሜትር መድረሱን ገልጸዋል፡፡
የክልሉ የመንገድ ሽፋን በ1985/86 ዓ.ም 8 ሺህ 507 ኪሎ ሜትር እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ዘጠኝ ድልድዮች ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆን፥ 4 ሺህ 298 ኪሎ ሜትር መንገድ መጠገኑን ነው ኢንጂነር ሔለን የገለጹት፡፡
ለዚህም 148 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ተናግረዋል።
በተጠናቀቀው ግማሽ በጀት ዓመት ቢሮው የዕቅዱን 123 ነጥብ 3 በመቶ መፈጸሙን እና ከ964 ሚሊየን ብር በላይ አገልግሎት ላይ ማዋሉን ተናግረዋል፡፡
የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ እና የጥገና ሥራዎች የተከናወኑት÷ በፌደራል እና በክልሉ መንግሥት እንዲሁም በህብረተሰቡ ተሳትፎ መሆኑንም የቢሮ ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡
በሌላ በኩል በሻሸመኔ ከተማ አንድ የተቀናጀ የአውቶቡስ መናኸሪያ መገንባቱም ተጠቅሷል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!