ቢዝነስ

የደብረ ብርሃን ከተማ 24 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ሰጠ

By ዮሐንስ ደርበው

February 23, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 24 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 188 አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የከተማዋ ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ብርሃን ገብረ ሕይወት፥ በማምረት ላይ ያሉ ሥድስት ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ 12 ሚሊየን 529 ሺህ ዶላር ማስገኘት ተችሏል ብለዋል፡፡

በቀጣዩ ግማሽ ዓመትም ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እና 24 ኢንዱስትሪዎች ምርት እንዲጀምሩ ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡

ሳያለሙ ለረዥም ጊዜ መሬት አጥረው የተቀመጡ ባለሃብቶችን በመለየት እርምጃ እንደሚወሰድም ጠቁመዋል፡፡

የውጭና የሀገር ውስጥ አልሚዎችን ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ የመሳብ ሥራ በትኩረት እንደሚከናወንም ነው አቶ ብርሃን የገለጹት፡፡

በዘላለም ገበየሁ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!