የሐረሪ ክልል በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ፡፡
በዞኑ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በርካታ ዜጎች ለጉዳት መዳረጋቸውን የተገለጸ ሲሆን ፥ የክልሉ መንግስት ለዜጎቹ የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይ አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
እየደረሰ የሚገኘውን ጉዳት ለመቀነስም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባ መገለጹን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡