የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

February 23, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶቢያስ ቢልስተሮም ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ፥ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አተገባበር እና እየተከናወኑ የሚገኙ የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ስራዎችን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡

ቶቢያስ ቢልስተሮም በበኩላቸው ÷ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አድንቀው ፤ ሀገራቸው ለስምምነቱ ተግባራዊነት ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያና ስዊድን መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሻሻል የተጀመሩ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!