የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሁለት ዘርፎች የ‘ስታት ትሬድ ታይምስ ካርጎ ልኅቀት ሽልማት’ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የዓመቱ የአፍሪካ ካርጎ አገልግሎት ሰጪ” እና “በአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የአየር ካርጎ ብራንድ” በሚሉ ዘርፎች የስታት ትሬድ ታይምስ ካርጎ ልኅቀት ሽልማት ማሸነፉን አስታውቋል።
አየር መንገዱ ሽልማቶቹን በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው ‘ኤር ካርጎ አፍሪካ 2023’ መርሐ ግብር ላይ መረከቡን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የስታት ታይምስ ሽልማት /The STAT Times Award/ በአየር የካርጎ አገልግሎት የላቀ ብቃት እና በኢንዱስትሪው ውስጥ ላስመዘገቡ የላቁ ስኬቶች እውቅና የሚሰጥ ዓለም አቀፍ ሽልማት ነው።