29ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 29 ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ “ዓድዋ አንድነት ጀግንነት ነፃነት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች ተሳታፊዎች በተገኙበት ለመወያያ የሚሆን መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይቱ እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ÷ ዓድዋ ኢትዮጵያውያን ስለነፃነታቸው የተዋደቁበት እና በአንድነት የተሰለፉበት ድል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ለድሉ መመዝገብ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡
ሀገር ስትነካ በጋራ መሰለፍና ድል ማድረግን አባቶች አስተምረው ነፃ ሀገር ማስረከባቸውን ይህ ትውልድ ሊገነዘብ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
የዓድዋ ድል በሀገር ግንባታ እና ሕዝቦችን በማስተሳሰር በኩል ያለው ሚና ግዙፍ መሆኑም ነው የተገለፀው።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ