ኢትዮጵያ 2ኛውን በሠራተኞች ላይ የሚመክር የሚኒስትሮች ጉባዔ እንደምታስተናግድ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሠራተኞች ፣ በሥራ እና ፍልሰት ላይ የሚመክረውን 2ኛውን የሚኒስትሮች ጉባዔ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደምታስተናግድ ተገለጸ፡፡
በኢጋድ አባል ሀገራት ውስጥ ሥራ እና የሠራተኞች ጉዳዮች ላይ የሚሠሩ ሚኒስትሮች በአንድ ላይ እንደሚሰባሰቡ እና ጅቡቲ የተፈረመው ስምምነት አፈጻጸም ላይ እንደሚመክሩ የዓለምአቀፍ የሠራተኞች ድርጅት መረጃ ጠቁሟል፡፡
የጅቡቲው ሥምምነት የሚያተኩረው ስደተኞች እና ልጆቻቸውን ማስተማር ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ጉባዔው በፈረንጆቹ መጋቢት 2 ቀን ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡