Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብትን  በፍትሃዊነት ለተቃሚዎች ለማድረስ እየሰራች መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የውሃ ሀብትን  በፍትሃዊነት ለተጠቃሚዎች ለማድረስ እየሰራች መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ተናገሩ፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና እርሻ  ድርጅት አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የብሔራዊ የውሃ ፍኖተ ካርታ ውይይት ኢትዮጵያ ተሞክሮዋን አካፍላለች፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ያቀረቡት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ  ÷ ኢትዮጵያ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓትን በማስፈን የውሃ ሀብት በፍትሃዊነት ለተቃሚዎች ለማድረስ እየሰራች መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር  እና የዉሃ እጥረትን መቋቋም የሚችል የክላስተር ስንዴ ተግባራዊ ማድረጓ ለውሃ ሀብት መበልፀግ አስተዋፅኦ ማድረጉንም አብራርተዋል፡፡

ከመንግስት በሚመደብ በጀትና በልማት አጋሮች በኩል በሚደረግ  ድጋፍ  ዜጎችን የንጹህ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በኢነርጂ ልማት ረገድ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ሃይል ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ የውሃ ሀይል በማመንጨት ለጎረቤት ሀገራት የማሰራጨት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን መናገራቸውን ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.