Fana: At a Speed of Life!

ዘመን ባስ በአዲስ አበባ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዘመን ባስ በአዲስ አበባ ከተማ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

የዘመን ባስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት መጨናነቅን ለመቅረፍ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው ያስታወቀው።

የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው ዘመን ባስ፣ ጎልደን ባስ፣ ሀበሻ ባስ እና የኛ ባስ አክሲዮን ማህበራት አውቶብሶቻቸውን በመመደብ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
ዘመን ባስም በአዲስ አበባ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት ርቀትን ጠብቆ ለመጓጓዝ የሚፈጠረውን የትራንስፖርት እጥረትና መጨናነቅ ለመቀነስ በማሰብ “ነፃ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ለአሳደገን ህዝብ” በሚል መሪ ቃል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በዚህም መነሻ መስቀል አደባባይ ስታዲየም ዙሪያ ሆኖ፥ መዳረሻ ቦታዎች ጦር ሀይሎች፣ አየርጤና፣ ሳር ቤት፣ መካኒሳ፣ ጀሞ፤ ተመላሽ በሃና ማሪያም ቃሊቲ፣ ከቃሊቲ ሳሪስ አቦ፣ ቦሌ፣ ሜክሲኮ ሳሪስ አቦ፣ ቦሌ፣ ሜክሲኮ፣ መገናኛ፣ ወሰን፣ ካራ፣ የካ አባዶ፤ ተመላሽ በመገናኛ፤ ቦሌ፤ ሳሪስ ቃሊቲ።

ከቃሊቲ በሳሪስ ስታዲየም- ሜክሲኮ – ሳሪስ – ቃሊቲ።

ተመላሽ እስከ ሜክሲኮ፣ አራት ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ፣ፒያሳ አዲሱ ገበያ።

አስኮ መንገድ መድኃኒዓለም እነዚህን ዋና ዋና መንገዶችን መነሻና መድረሻ በማድረግ ስምሪቱ እንደ አካባቢው ትራንስፖርት እጥረት የሚስተካከል ከሚያዚያ 1 ቀን ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናቶች በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ አክሲዮን ማህበሩ ገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.