Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ የድህረ አገልግሎት ክፍያ ስርዓት ሊዘረጋ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ የድህረ አገልግሎት ክፍያ ስርዓት ሊዘረጋ መሆኑን አስታወቀ።

አገልግሎቱ ከደንበኞቹ የሚሰበስበውን ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።

አዲሱ ስርዓት አሰራርን ከማዘመን በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ታልሞ መዘጋጀቱም ነው የተገለፀው።

ተቋሙ በቅርብ ተግባራዊ ያደረገውን የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲስተም ጋር በማስተሳሰር የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያውን ከ1 ሺህ 585 በላይ በሚሆነው የባንኩ ቅርንጫፎች መክፈል የሚያስችል አምስት አማራጮችን ዘርግቷል።

እነሱም በንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመሄድ የሚፈፀም የጥሬ ገንዘብ ክፍያ፣ ከቀጥታ ሂሳብ ተቀናሽ ተደርጎ የሚፈፀም ክፍያ፣ በእጅ ስልክ አማካኝነት እና በኢንተርኔት እና ሞባይል ባንኪንግ የሚከፈሉ ናቸው።

ከሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮም ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ነው የተባለው።

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.