ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሊደረጉ የነበሩ ሁለት ጨዋታዎች ተራዘሙ

By Mikias Ayele

February 25, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ ሊደረጉ የነበሩ ሁለት ጨዋታዎች መራዘማቸውን ሊግ ካምፓኒው አስታውቋል፡፡

ጨዋታዎቹ በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ነው የተራዘሙት፡፡

በ15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቀን 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የጀመሩት ሲዳማ ቡና እና ኢትዮ ኤሌትሪክ በድሬዳዋ ስታዲየም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ጨዋታቸውን አቋርጠዋል፡፡

በድሬዳዋ ያለውን የአየር ንብረት ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትም አክሲዮን ማህበሩ ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ እንዲራዘም ወስኗል፡፡