Fana: At a Speed of Life!

የበጋ መስኖ ስንዴ አበረታች ውጤት ታይቶበታል- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ እየለማ የሚገኘው የበጋ መስኖ ስንዴ አበረታች ውጤት የታየበት መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ አርሶ አደሮች የተሣተፉበት ክልላዊ የአርሶ አደሮች የመስክ ምልከታ በባምባሲ ወረዳ ተካሂዷል፡፡

በባምባሲ ወረዳ መንደር 40፣ መንደር 44 እና ዳቡስ ቀበሌዎች በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ተጎብኝቷል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ባበክር ኻሊፋ በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት÷ በተያዘው የበጋ ወቅት 2 ሺህ 500 ሔክታር መስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ የዕቅዱን 97 በመቶ ማሣካት ተችሏል።

በክልሉ ባምባሲ፣ ኡራ እና አቡራሞ ወረዳዎች በበጋ መስኖ የተሻለ መፈጸማቸውን ጠቅሰዋል።

በ2015/16 የመኸር እርሻ 50 ሺህ ሔክታር በዘር ለመሸፈን ዝግጅት እየተደረገ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.