Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት አገልግሎቱ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋገጥ መልኩ መሆን አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋገጥ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት በሚያግዝ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የትራንስፖርትና ሎጂስቲከስ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ የሥድስት ወር እቅድ አፈፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡

በግምገማው ላይ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት፣ የተለያዩ ስትራቴጂዎችንና ህጎች በማዘጋጀትና ሥራ ላይ በማዋል የትራንስፖርትናሎጂስቲከስ ዘርፉን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት መገኘቱ ተገልጿል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲከስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ÷ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋት እና ለዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም ነው የተገለጸው፡፡

የነዳጅ ድጎማ አሰራርን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

ህዝብን ማዕከል ያደረገ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር ለትራንስፖርት ተጠቃሚው ማህብረሰብ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች እስከ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች በመውረድ ጥብቅ ክትትልና ግምገማ በማድረግ ለውጥ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.