የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

By Alemayehu Geremew

February 27, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት በርዕሠ መስተዳድሩ እንደሚቀርብ ተመላክቷል ፡፡

በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በመስክ የተገመገሙና በካፒታል በጀት የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችም ገለፃ እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ፥ ያለፉት ሥድሥት ወራት አፈፃፀምን ካቀረቡ በኋላ በምክር ቤቱ እንደሚያፀድቁ ም ይጠበቃል።

በኢዮናዳብ አንዱዓለም