Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ግርማ አመንቴ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ የግብርና ዘርፍን ለማዘመን በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ ቻይና የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን በምታደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ቻይና በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ድጋፍ እንደምታደርግ ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራም በውይይቱ መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.