Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ መደበኛ 6ኛ የስራ ዘመን 2ኛ ዓመት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
 
የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በስብሰባው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል ፡-
 
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ህዝብ ኑሮና ተጠቃሚነት በመሰረታዊነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ፈጣን፣ ዘላቂና ሰፊ መሰረት ያለው ልማት በማስመዝገብ የተለያዩ የልማት ስትራጂዎችን በማመንጨት ስትራቴጂዎቹን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችንና አሰራሮችን በመዘርጋት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
 
ባለፉት ዓመታት ውስጥ የህዝባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የከተማ ልማት ለማካሄድ በከተመዎቹ የእድገት ደረጃ መሰረት በርካታ ከተሞችን በመመስረት ሰፋፊ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁን በደረስንበት የእድገት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ በመሆን ህዝባችንና ክልላችን የሚመጥኑ ከተሞችን ለመፍጠር እንዲሁም ህገ ወጥነትን በመቆጣጠር በከተሞች ውስጥ እየታዩ ያሉ ውስብስብ ሁኔታዎችን ለማስተዳደር ያለውን አደረጃጀት እየፈተሹና እያሻሻሉ መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡
 
በመሆኑም ከተሞቹ ያላቸውን መልካም እድል ወደ አንድ በማምጣት አብሮ እንዲለሙና የጋራ ዓላማ እንዲኖራቸው፣ በአንድ ፕላን በመተዳር ሁለንተናዊ እድገት እንዲኖራቸው፣ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት ኖሯቸው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ሙያን ለማስፋፋት፣ የብዝነስ አስተሳሰብን ለማዳበር እና የአገልግሎትን ለማሻሻል የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ሁለትና ከዛ በላይ ከተሞችን አንድ ላይ ለማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ለአስተዳደር በሚያመች መንገድ የከተሞቹ አደረጃጀት እንደሚከተለው ተከናውኗል፡፡
 
1. ቢሾፍ ከተማ፡ የቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እንዲሁም የመዘጋጃ ቤት ከተሞች ሂዲ፣ ኡዴ ደንካካ እና ድሬ በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ10 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
 
2. ሻሸመኔ ከተማ፡ የሻሸመኔ ከተማ እና የብሻን ጉራቻ ከተማ በመቀላቀል በ4 ክ/ከተሞች እና በ12 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
 
3. አዳማ ከተማ፡ የአዳማ ከተማ እና የወንጂ ከተማን በመቀላቀል በ6 ክ/ከተሞች እና በ19 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
 
4. ሮቤ ከተማ፡ የሮቤ ከተማ እና የጎባ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
 
5. ማያ ከተማ፡ የሀረማያ ከተማ፣ የአወዳይ ከተማ እና የአዴሌ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
 
6. ባቱ ከተማ፡ የባቱ ከተማ እና የአዳሚ ቱሉ ከተማን በመቀላቀል በ7 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
 
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የመልማት እድል ያላቸው ከተሞቻን በተሟላ መንገድ በመጠቀም ሁለንተናዊ የሆነ ልማት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞችማ ወረዳዎችን ልማት እንዲያፋጥኑ ለማድረግና የአመራን ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል የሚከተሉት ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ተወስኗል፡፡
 
1. መቱ ከተ
 
2. መቱ ከተ ከተማ
 
3. ቡሌ ሆራ ከተማ
 
4. ነጆ ከተማ
 
5. ሰንዳፋ በኬ ከተማ
 
6. ሸኖ ከተማ
 
7. ሞያሌ ከተማ
 
8. ዶዶላ ከተማ
 
9. ሻክሶ ከተማ
 
በተመሳሳይ መልኩ የከተሞች የማስፈፀም አቅማቸው ተሻሽለው ፈጣንና ከእንግልት የፀዳ አገልግሎት በሙሉ አቅም እንዲሰጥና ሁሉ አቀፍ የሆነ ልማት እንዲመዘገብ ለማድረግ እንደ አጠቃላይ እየተደረገ ያለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣዎን የከተሞችን እድገት መሠረት በማድረግ የከተሞችን ደረጃ እንደሚከተለው እንዲሻሻል ተወስኗል።
 
1. አዳማ፣ ሻሻመኔና ቢሾፍቱ ከተሞች፡- የሬጂዮ-ፖሊስ ከተማ
 
2. የሮቤ ከተማና የማያ ከተማ፡- ዋና ከተማ
 
3. የመቱ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌና ሻክሶ ከተማ፣- ወደ ከፍተኛ ከተማነት እንዲያድጉ ተወስኗል።
 
በሌላ መልኩ ለረጂም ጊዜ ስነሳ የቆየውን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ፈጣን የሆነ የኢኮኖሚያና ማህበራዊ ለማስመዝገብ፣ በድንበር አካባ ያለውን ህገ ወጥነትን ለመቅረፍ፣ በድንበር አካባ ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚከሰተውን የሰላም ሁኔታን ለመፍታት እንዲሁም ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለማቅረብ ውጤታማ የሆነ አደረጃጃትና አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የምስራቅ ቦረና ዞን አዲስ ዞን ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል፡፡
 
በአዲስ መልክ 21ኛ ዞን ሆኖ የተደራጀው የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና ከተማው ነጌሌ ቦረና ሆኖ፡-
 
• ከቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ፣ ሞያሌ ከተማ፣ ጉቺ ወረዳ እና ዋችሌ ወረዳ፣
 
• ከጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ፣ ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ፣ ነጌሌ ቦረና ከተማ፣
 
• እንዲሁም ከባሌ ዞን መደወላቡ ወረዳ፣ ኦቦርሶ ወረዳ እና ሀረና ቡሉቅ ወረዳ በመጨመር እንደ ዞን 10 ወረዳዎችን በመያዝ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡
በአዲሱ አደረጃጀት የምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጆ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል ፡፡
 
በልላ በኩል ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሆነ አደረጃጀት ለመፍጠር የመሬት ስፋት፣ የፀጥታ ችግር የመልካም አስተዳደር ጥያቄና ፈጣን ልማት ጥያቄን ለማረጋገጥ የመደ ወላቡ ወረዳ የነበረ በሁለት ቦታ ማለትም የመደ ወላቡ ወረዳና ኦቦርሶ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅና የጭናክሰን ወረዳ የነበረ በሁለት ወረዳ ማለትም የጭናክሰን ወረዳና የመከኒሳ ኦሮሞ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.