የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከሀገር የሚያስበልጡት አጀንዳ ያለመኖሩን የሚያሳይ ነው – የታሪክ ምሁራን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከሀገር የሚያስበልጡት አጀንዳ አለመኖሩን የሚያሳይ እንደሆነ የታሪክ ምሁራን ገለጹ፡፡
ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሃፊ ተሾመ ብርሃኑ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ ፣ ለአፍሪካውያን ደግሞ ፍርሃትና ጭንቀትን ያስወገደ ድል ነበር ብለዋል፡፡
የጥናትና ምርምር ባለሙያው ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል በበኩላቸው ÷ የዓድዋ ዘመቻ አፍሪካውያንን ከተኙበት ያነቃ ፤ የመቻል አቅምንም ለዓለም ያሳየ እንደነበር አንስተዋል፡፡
የዓድዋ ድል ምክንያትም የህዝቦች አንድነት እንደነበር ነው ያወሱት፡፡
የአፍሪካውያንን አንገት ቀና ያደረገ፤ የጥቁር ሕዝቦችን ነጻነትን ያወጀ ፤ድንቅ ክስተት እና የነጻነት ምልክት ነውም ብለዋል ምሁራኑ፡፡
በሃይማኖት ወንዲራድ