Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት የቻይናን የሰላም እቅድ መደገፍ ይገባዋል ሲሉ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት የቻይናን የሰላም እቅድ መደገፍ ይገባዋል ሲሉ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን አሳሰቡ፡፡

የሃንጋሪ መንግስት በዩክሬን ውስጥ ለቀጠለው ግጭት የቤጂንግን የሰላም እቅድ ይደግፋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በትናንትናው ዕለት ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል።

ባለፈው ሳምንት በቻይና የቀረበው ባለ 12 ነጥብ የሰላም ድርድር እቅድ የአንድ ወገን ማዕቀቦችን በማውገዝ የሁሉም ሀገራት ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ተከብሮ እንዲቀጥል ይጠይቃል።

ቪክቶር ኦርባን “ የቻይናን የሰላም እቅድ አስፈላጊ አድርገን እንቆጥረዋለን፣ እንደግፋለን” ሲሉ ለሃገሪቱ ህግ አውጪ አካላት መናገራቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

የሩሲያ-ዩክሬን ግጭት ለዩክሬናውያን፣ ሩሲያውያን፣ ሃንጋሪያውያን እና አውሮፓውያን ብሎም ለመላው ዓለም አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም ቡዳፔስት በብሔራዊ ምክክር በተወሰነው መሰረት ከግጭቱ መራቅ እንዳለባት አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.