Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝና ዴንማርክ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚከናወነውን ስራ እንደሚደግፉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ ከዴንማርክ አምባሳደር ኪራ ስሚዝ ሲንድቢየርግ እና ከእንግሊዝ የልማት ትብብር ዳይሬክተር ፓውል ዋልተር ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ተሾመ÷ በኮሚሽኑ ዓላማዎች፣ ፕሮግራም መሰረት ያደረጉ ዋና ዋና ግቦች እና በተልዕኮው ስኬት የልማት አጋሮች ሚና ዙሪያ ገላጻ አድርገዋል፡፡

በምክክሩ ሁለቱ ሀገራት ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጅምሮች እና የተሃድሶ ኮሚሽን ስራዎችን እንደሚደግፉ አንስተዋል፡፡

በተለይ በሰላም ስምምነቱ መሰረት የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋምና የሰላምና የልማት አካል ለማድረግ የሚያደረገውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ማረጋገጣቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.