127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ይከበራል፡፡
በዓሉን ምክንያት በማድረግም 21 ጊዜ ከማለዳው 12:00 ሰዓት መድፍ እንደሚተኮስ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።