Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ዛሬ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሎሚ ሜዳ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ሁለት ሼዶች መውደማቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡

በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በአደጋው የአምስት ልብስ ስፌት ማኅበራት ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠርም አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከ69 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጋር መሠማራቱን ጠቁመዋል፡፡

የእሳት አደጋው ተስፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ነው አቶ ንጋቱ የገለጹት፡፡

ረፋድ 5 ሰዓት ከ15 ላይ በተከሰተው አደጋ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ እና አደጋውን ለመቆጣጠርም አንድ ሰዓት መፍጀቱን አመላክተዋል፡፡

ሎሚ ሜዳ ወይም ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ የሚጠራው ይህ የማምረቻ ስፍራ በከተማ ደረጃ ለአደጋ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ ቦታዎች አንዱና በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ የሚከሰትበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.