Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት ክፍሎች የዓድዋ ድል በዓልን በተለያዩ ዝግጅቶች አከበሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ክፍሎች 127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በፓናል ውይይት እና በሌሎች ዝግጅቶች አከበሩ፡፡

ትውልዱ የአያቱን የጀግንነት ታሪክ አስጠብቆ ታሪክን ለትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት በውይይቱ ላይ መገለጹን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የድል በዓሉን ያከበሩት÷ የምስራቅ ዕዝ እና የደቡብ ዕዝ የስታፍ የሰራዊት አመራርና አባላት፣ የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የሰራዊት አባላት እና የሲቭል ሰራተኞች፣ የመከላከያ ዩንቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ አመራርና አባላት ናቸው፡፡

በተጨማሪም በሶማሊያ የሴክተር ሶስት ሰላም አስከባሪ ሰራዊት፣ በአትሚስ ሴክተር 4 ሰላም አስከባሪ ኃይል ሁሉም ሻለቆች እና ሌሎችም የመከላከያ ክፍሎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

127ኛው የዓድዋ የድል በዓል “ዓድዋ አንድነት፤ ጀግንነት እና ፅናት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

#Ethiopia #Adwa #Victory

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.