Fana: At a Speed of Life!

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ አንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት” በሚል መሪ ሐሳብ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተከብሯል፡፡

የድል በዓሉ የተቋሙ ዋናው መስሪያ ቤት የሠራዊቱ አባላት በተገኙበት በፓናል ውይይት መከበሩን ከፌደራል ፖሊስ ያገነኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ባደረጉት ንግግር÷ በዓሉን ስናከብር ሀገሪቱን ወደ ብልፅግና ማማ ለማውጣት ለሚደረገው ጥረት አቅም ለመሆን ከዓድዋ ብዙ ስንቅ እና አቅምን ለመውረስ ነው ብለዋል።

ዓድዋ ትልቅ ክብር የሚሰጠው በዓል ስለሆነ ተጨማሪ አኩሪ ታሪኮችን እየፈፀምን ወደፊት የምንጓዝበት ጊዜ ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።

በዓድዋ የጦርነት ታሪካዊ ዳራ ላይ ያጠነጠነ የመነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

#Ethiopia #Adwa #Victory

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.