የሀገር ውስጥ ዜና

የዓድዋ የድል በዓል የኢትዮጵያውያንን የሞራል ልዕልና ያበለጸገ ነው- ዶክተር አብርሃም በላይ

By ዮሐንስ ደርበው

March 01, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ የድል በዓል የኢትዮጵያውያንን የሞራል ልዕልና ያበለጸገና ጠንካራ መሰረት ላይ ያኖረ በመሆኑ በአንድነት መንፈስ በድምቀት ልናከብረው ይገባል ሲሉ ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ ዓድዋ በወቅቱ የነበረውን የዓለም የኃይል እና የእሳቤ ዝንባሌ ድምዳሜዎች ትልቅ ጥያቄ ውስጥ የከተተ የተጋድሎ ውሎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

አዲሱ ትውልድም ታሪክን በወቅቱ ከነበረው ዓውድና እውነታ ባፈነገጠ መልኩ ለሰፈርና ለመንደር እያሰበ ከመተንተንና ከመነታረክ መውጣት አለበት ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም፡፡

በመሆኑም ትውልዱ ለነፃነትና ሉአላዊነት በአንድነት የተከፈለውን መስዋእትነት ሳያሳንስ በአሉን በኢትዮጵያዊነት መንፈስና ልክ እንዲያከብርም ጠይቀዋል፡፡

የዓድዋ ድል ህያው ድል ስለሆነ ከታሪክነቱ ባለፈ ዛሬን የመዋጃ ነገንም የማቅኛ መሪ ስንቅ በመሆኑ÷ በድሉ ትርጉምና ፋይዳ ዙሪያ ለዚህ ትውልድ የጠራ ትምህርት ሊሰጥበት እንደሚገባም ነው በአጽንኦት ገለጹት፡፡

#Ethiopia #Adwa #Victory

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!