የሀገር ውስጥ ዜና

የከተማ አስተዳደሩ ለ6 ክልሎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

April 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለ6 ክልሎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

የከተማ አስተዳደሩ በሁለተኛው ዙር የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ከነገ ጀምሮ ለትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ክልሎችእንዲሁም  ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደደር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ለክልሎች የሚሰራጩት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የከተማ አስተዳደሩ በራሱ በጀት የገዛቸው ሲሆን በዋነኛነት ለህክምና ባለሙያዎች የሚሆኑ የፊትና ሰውነት መሸፈኛዎች፣ ጓንትና ሳኒታይዘሮች እንዲሁም ሌሎች የንጽህና መጠበቂያዎች ይገኙበታል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና ለቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እንዲሆን ባለፈው ሳምንት ለሶስት ክልሎች ለእያንዳንዳቸው 15 ሚሊየን ብር የሚገመት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመላክታል።