Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን ያጋጠመውን የውሃ ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በቦረና ዞን ያጋጠመውን የውሃ ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ የአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ፥ ድጋፉ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የቦቆሎ ዱቄት፣ ሩዝ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ጨውና ሌሎች ቁሳቁሶች በድጋፉ ተካተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ፥ አሁን የተደረገው ድጋፍ በቂ ባይሆንም የድርሻችንን ለመወጣት ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት ከራስ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ ማህበረሰብ አሁን በድርቁ ጉዳት እንደደረሰበትም ነው የገለጹት፡፡

ሆኖም በዞኑ የገጠመው ድርቅ ከሁለት እና ሦስት ዓመት በሁዋላ ታሪክ ሆኖ እንዲቀር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.