Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የታክስና የጉምሩክ ሕግ-ተገዢነት ንቅናቄ መክፈቻ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የታክስ እና የጉምሩክ ሕግ-ተገዢነት ንቅናቄ መክፈቻ መርሐ-ግብር በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
መርሐ ግብሩ ”ግብር፤ ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የንቅናቄ መድረኩ ግብር ከፋዩ ግብርን በአግባቡ እንዲከፍል ለማስቻልና ሕገ-ወጥነትን ለመከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤ ስራዎችን ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።
ሕገ-ወጥነትና የኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚደርሱትን ጉዳት በጋራ ለመከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤ ስራዎች በንቅናቄው እንደሚከናወኑም ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሤ ÷ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ተከብራ እንድትቀጥል ግብር ከፋዮች ለሀገራቸው ታማኝ በመሆን አዲስ የአድዋ ድል ምዕራፍ መጻፍ እንደሚገባቸው ገልጸል፡፡

ዓድዋ ከኢትዮጵያም ባለፈ ለአፍሪካ ታላቅ የኩራት ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው÷ቀደምት አያቶቻችን ኢትዮጵያን ከነክብሯ ለማቆየት ያሳዩትን አንድነት፣ ጀግንነትና ፅናት በመውረስ የአሁኑ ትውልድ ግብርን ለሀገር ክብር መክፈል ይኖርበታል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ከ450 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን እና ባለፉት ሰባት ወራት ከ258 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ካላት አቅም አንጻር የሚገባትን ገቢ ለመሰብሰብ የግብር ከፋዩ ታማኝነት፣ የአስፈጻሚ አካላት ቁርጠኝነትና ቀልጣፋ አሰራር ሊኖር ግድ ይላልም ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.