Fana: At a Speed of Life!

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች 127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የፓኪስታን መንግስት አመራሮች፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ተከብሯል፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር÷የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ጀግና አርበኞች በተባበረ ክንድ ቅኝ ገዢዎችን በማንበርከክ ታሪክ የሰሩበት ነው ብለዋል፡፡

ዓድዋ የአንድነት፣ የጀግንነት፣ የጽናት እና የአልደፈር ባይነት ተምሳሌት ነው ያሉት አምባሳደሩ÷ይህም ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቁ ቅኝ ገዢዎችን ማንበርከክ አስችሏል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ÷የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ ለአፍሪካ ብሎም ለመላው አለም የነጻነት ጎህን የቀደደ፣ የአልገዛም፣ አልበገርም፣ የእምቢ ለሀገሬ ባይነት መንፈስን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ያጎናጸፈ የብቃት ምልክት ነው ብለዋል።

በጀቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲም 127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቅት አክብሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.