የህንድ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ ከህንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ አክሊሉ÷ የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በመሰማራት የሀገራቱን የቆየ ወዳጅነት ከማጠናከር ባለፈ በስራ እድል ፈጠራ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ በርካታ የህንድ ባለሃብቶች ገብተው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ለማድረግ የሚያስችሉ የማሻሻያ ስራዎችን እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ሽሪ ሮበርት በበኩላቸው÷ የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በሁሉም ቦታዎች ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችን ፈጥረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡
በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው÷ በቀጣይም ተጨማሪ ባለሃብቶች ገብተው መዋዕለ ንዋያቸውን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡
የህንድ ባለሃብቶች በበርካታ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በመሰማራት ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠራቸውንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡