Fana: At a Speed of Life!

ከ80 በላይ የፓኪስታን ባለኃብቶች ልዑክ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ80 በላይ የፓኪስታን ባለኃብቶችን ያቀፈ የንግድ ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ገለጹ።

 

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ከፓኪስታን ወደ ኢትዮጵያ ስለሚመጣው የንግድ ልዑክ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

 

የንግድ ልዑኩ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እድልና አማራጭ ለመጠቀም እንደሚመጣ አምባሳደሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

 

ለዚህም÷ በግብርና፣ በማምረቻ፣ በማዕድን፣ በቴክኖሎጂ፣ በጤናና በሌሎች ዘርፎች የተሰማራ የፓኪስታን የንግድ ልዑክ በመጭው እሁድ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ ተናግረዋል።

 

የንግድ ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ የአንድ ሳምንት ቆይታ እንደሚያደርግም ነው የገለጹት፡፡

 

ልዑኩ በቆይታው በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችንና የመስህብ ስፍራዎች ላይ ጉብኝት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.