Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዳሰነች ለሚገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚገነባው የኦሞራቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድጋይ አስቀመጡ ።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አለማየሁ ባውዲና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 20 ሚሊየን ብር ሲሆን÷ በደቡብ ክልል መንግስት እና “ሰው ለሰው” በተሰኘ ግብረ-ሠናይ ድርጅት በጋራ እንደሚሸፈን ተገልጿል ።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም በመርሐ ግብሩ ላይ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.